Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በ2016 በጀት ዓመት ለሆስፒታላችን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የኦከስጅን ማሽን ዓመታዊ ዕድሳት (Annual Service) በግልጽ ጨረታ ማሳደስ /Service/ ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

Image
img
Free
Ref No
Company Info
Published On
Region
Tender Category
Contact Phone
Contact Email
Remaining Date
Bid Open Date
Bid Close Date
Publish Date
Bid Bond
Bid Type
Tender Doc Price

አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አዩ/ግአ/007/2016

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በ2016 በጀት ዓመት ለሆስፒታላችን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የኦከስጅን ማሽን ዓመታዊ ዕድሳት (Annual Service) በግልጽ ጨረታ ማሳደስ /Service/ ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት በጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የTIN የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) በላይ የሚያወጣ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ሙሉ ዕድሳት ለማድረግ ዋጋ ከመሰጠቱ በፊት ማሽኑ የሚገኝበት ሪፈራል ሆስፒታል በአካል በመገኘት አጠቃላይ ችግሩ ከተለየ በኋላ ዋጋው መሞላት አለበት፡፡

4. የዕድሳት አገልግሎት ለማከናወን የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ወጪ እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ዋጋ አሸናፊ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡

5. አሸናፊው ዕድሳቱ ተጠናቆ ክፊያ ከተፈፀመበት አንድ ዓመት የሚቆይ ዋስትና (Guarantee) ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ውል ይፈርማል፡፡

6. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለተሸናፊዎች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በሲፒኦ አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ በራሳቸው የዋጋ መሙያ ወይም ሆስፒታሉ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡

9. ተጫራቾች ዋጋ የሚሞሉበትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ኤንቬሎፕ አድርገው እስከ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ግዥ የሥራ ክፍል ለዚሁ በተጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

10. የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን በ3፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት በግዥ የሥራ ክፍል ይከፈታል፡፡

11. ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

12. ሪፈራል ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917076093 ይጠቀሙ::

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል

No clarification Available

# Lot Price Lot Number Action