Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Image
img
Free
Ref No
Company Info
Published On
Region
Tender Category
Contact Phone
Contact Email
Remaining Date
Bid Open Date
Bid Close Date
Publish Date
Bid Bond
Bid Type
Tender Doc Price

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2017ዓ.ም

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

የዕቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ

ሎት 1

አላቂ ቢሮ እቃ

5000.00

ሎት 2

የህክምና እቃ

2,000.00

ሎት 3

አላቂ የትምህርት እቃ

7000.00

ሎት 4

አላቂ የጽዳት እቃ

8000.00

ሎት 5

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

3,000.00

ሎት 6

ማሽነሪና እና ለመሳሪያ እድሳት

2,000.00

ሎት 7

ለተገጣጣሚ እድሳት

5,500.00

ሎት 8

ለፕላንት እና ማሽነሪ

7,500.00

ሎት 9

ለህንጻ ቁሳቁስ ለተገጣጣሚ

8,500.00

 ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር (TIN No) ሊኖራቸውና ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ለሚያቀርቡት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እና የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፣
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ አርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በተዘረዘሩት ሎት መሰረት ለእያንዳንዳቸው የዋጋ ማስከበሪያ በተጠቀሰው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) መክፈል በለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናል ኮፒ ብለው በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  9. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
  10. መስሪያ ቤቱ የሚገዛው እቃ ላይ 20% መጨመር እና መቀነስ ይችላል።
  11. ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 67-76 35 ወይም በአካል ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ሰሚት ኮንደሚኒየም 3ኛ በር ገባ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ትንሽ ወረድ ብሎ ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

No clarification Available

# Lot Price Lot Number Action

Compare Products

Clean All Start Comparing !