Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት እና አጋሮች በሳንባ በሽታ መከላከል የተሻለ ለውጥ ላስመዘገቡ የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲቀጥሉ ጠየቀች

Blog

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት እና አጋሮች በሳንባ በሽታ መከላከል የተሻለ ለውጥ ላመጡ የአፍሪካ አገራት ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበች።


የሳንባ በሽታን አስመልክቶ የተዘጋጀው የአፍሪካ ቀጣናዊ ስብስባ በታንዛንያ አሩሻ ተካሄዷል።

በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ልዑካን ቡድን በስብስባው ላይ ተሳትፏል።


ስብሰባውን ያዘጋጀው ‘ግሎባል ፈንድ ቱ ፋይት ኤድስ፣ቲዩበርኪሎሲስ ኤንድ ማላሪያ” የተሰኘው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ እና ትብብር ተቋም ነው።


በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት እ.አ.አ በ2030 የሳንባ በሽታን ለማጥፋት የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።


የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ኢትዮጵያ የሳንባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባከናወነችው ስራ አስደናቂ ለውጥ አምጥታለች ብለዋል።


በተለይም ኢትዮጵያ መድኃኒት የሚቋቋም የሳንባ በሽታን የመከሰት እና በበሽታው የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ በሽታው ከፍተኛ ጫና ካለባቸው የአፍሪካ አገራት ዝርዝር ውስጥ መውጣቷ ካስመዘገበቻቸው ስኬት በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።

‘ግሎባል ፈንድ ቱ ፋይት ኤድስ፣ቲዩበርኪሎሲስ ኤንድ ማላሪያ”፣ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና ሌሎች አካላት እ.አ.አ በ2030 የሳንባ በሽታ መከሰትን በመቀነስ ሂደት በጥሩ መንገድ ላይ ለሚገኙ አገራት ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።


“ኢትዮጵያ የሳንባ በሽታን በመከላከል ያገኘቻቸው መልካም ለውጦች በፋይናንስ ድጋፍ ቅነሳ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ገጥሞታል፤ ይህም በሳንባ በሽታ የተቀመጡ ግቦች ላይ መድረስን አስቸጋሪ አድርጎታል” ብለዋል።


ኢትዮጵያ በአሩሻ አዋጅ አማካኝነት እ.አ.አ 2030 የሳንባ በሽታን ለማጥፋት የተያዘውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ሚኒስትር ዴኤታው መግለጻቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

source:ENA ethiopian news agency